HIV - Support and Understanding (Amharic)

በኤች አይ ቪ/ኤድስ ተይዞ መኖር

፩.በኤች አይ ቪ/ኤድስ ተይዞ መኖር ወይም የሚወዱት ሰው በኤች አይ ቪ/ኤድስ መያዙን የምናውቅበት ጊዜ አስችጋሪ ወቅት ነው። ፪.በተጨማሪ በተለየ ቋንቋና ባህል ውስጥ መኖር ችግሩን የበለጠ ከባድ ያደርገዋል። ፫.የሚያሳስቦትን ችግር ከሌላ ሰው ጋር መወያየትና ጭንቀቶን ለሌሎች ማካፈል ችግሮን ያቃልልሎታል፤ ከግራ መጋባትም ያድኖታል።

የሚረዳዎት ሰው ወይም ክትትል እንዲደረግሎት ይፈልጋሉ:

  • ስለ እርሶ ወይም ስለሚንከባከቡት ሰው የጤና ሁኔታ እንዲብራራሎትና ግልጽ እንዲሆንሎት የሚፈልጉት ጉዳይ አለ?
  • ስላሉበት ሁኔታና ስለሚያሳስቦት ነገር ሰው ማነጋገር ይፈልጋሉ?
  • ቤተሰቦችዎ ያሉበትን ሁኔታ እንዲገነዘቡሎት ይፈልጋሉ?
  • የህክምና ባለሙያ ወይም የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኛ የእስዎን ፍላጎት እንዲረዱሎት ይፈልጋሉ?
  • ወደቀጠሮ ቦታ አብሮዎት የሚሄድ ሰው ይፈልጋሉ?

የመልቲ ካልቸራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ እና ሄፒታይተስ ሲ አገልግሎት የሚያስፈልጎትን እርዳታ ሊሰጦት ይችላል። ወንዶች ወይም ሴቶ የእርዳታ ሰራተኞች አሉን። ሰራተኞቻችን የእስያ የአፍሪካ የአውሮፓ የደቡብ አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ባህልና ቋንቋ ከመረዳታቸውም ባሻገር በኤች አይ ቪ/ኤድስ ተይዞ መኖር እንዴት እንደሚቻል ከባህሎ ጋር በማዛመድ እርዳታ መስጠት ይችላሉ። የእርዳታ ሰራተኞቻችን ያልተቆጠበ እርዳታ ይሰጣሉ እርሶ ማግኝት የሚገባዎትን አገልግሎቶች እንዲያገኙ ያደርጋሉ። ከረዳት ሰራተኞቻችን ጋር ቀጠሮ በመያዝ ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።

ለመሆኑ ያለሁበትን ሁኔታ ሊያውቅ የሚችለው ማን ነው?

ረዳት ሰራተኛው የራስዎ ባህልና ቋንቋ ተናጋሪ ቢሆን ምናልባት የእኔ የግል ጉዳይ በራሴ ማህበረተሰብ ውስጥ ይታወቃል የሚል ስጋት ያድርቦት ይሆናል።

መልቲ ካልቸራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ እና ሄፒታይተስ ሲ አገልግሎት የእርሶን የግል ሚስጢር ለመጠበቅ የሚከተሉንት እርምጃወች ይወስዳል፡

  • እርዳታ በሚፈልጉበት ጊዜ ትክክለኛ ስሞን የግድ መጠቀም የለቦትም
  • ረዳት ሰራተኞቻችን ያለእርስዎ ፈቃድ የእርሶን ሚስጢር ከማንም ጋር መነጋገር አይችሉም።
  • ረዳት ሰራተኞቻችን በመላው አውስትራሊያ የሚገኙ የጤና ባለሞያወች በሚተዳደሩበት ህግ መሰረት የሚመሩ ከመሆናቸውም ባሻገር ህጉን ተላልፈው ቢገኙ ከፍ ያል ቅጣት እንደሚጠብቃቸውም ያውቃሉ።
  • ያለ እርስዎ ሙሉ ፈቃድ የእርስዎን ምንም አይነት መረጃ (information) ለማንኛውም ድርጅት አሳልፈን አንሰጥም።/li>
  • ረዳት ሰራተኞቻችን በተለያየ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው የሚሰሩ ናቸው እንጂ በህብረተሰብ ውስጥ በኤች አይ ቪ/ኤድስ ሰራተኝነታቸስ ብቻ የሚታውቁ አይደሉም። ይህም የእርሶን የግል ሚስጥር ለመጠበቅ ይረዳቸዋል።

ህብረተሰቡ ውስጥ የሚኖሩ አንድ አንድ ሰዎች በኤች አይ ቪ/ኤድስ የተያዙ ሰዎች ላይ ያለምክንያት ጥላቻ ሊያድርባቸው ይችላል። ረዳት ሰራተኞቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ ርህራሄ የተሞሉ ለመሆናቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ የተመረጡ ሲሆን አስፈላጊውም ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። አስታውሱ አሁንም የግል ምስጥሮ ጉዳይ የሚያሳስቦት ከሆነ ከራስዎ ሃገር እና ባህል ውጪ የሆነ ረዳት ሰራተኛ እንዲሰጦት መጠየቅ ይችላሉ።

መብትዎ

በምንሰጠው አገልግሎት ተጠቃሚ እንደ መሆኖ መጠን ፍላጎቶ ተከብሮና ሚስጥሮ ተጠብቆ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ የመሆን መብት አሎት። በመልቲ ካልቸራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ እና ሄፒታይተስ ሲ አገልግሎት የሚገባውን እንክብካቤ እንዳላገኙ ከተሰማዎት ቅሬታዎትን የማሰማት መብት አለዎት። ቅሬታዎንም ለመልቲ ካልቸራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ እና ሄፒታይተስ ሲ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ በስልክ ወይም በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።

ለዚህ አገልግሎት ክፍያው ምን ያህል ነው?

እርሶን የሚያስከፍሎት ምንም ነገር የለም። የሜዲኬርም ካርድ ሆነ ሌላ የምንፈልገው መታውቂያ የለም።

እንዴት ግኑኝነት መ መር እችላለሁ?

እርስዎ ራስዎ፣  ኪሞ ወይም የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኛ (ሶሻል ዎርከር) በስልክ ቁጥር (02) 95151234 በስራ ሰዓት በመደወል ማነጋገር ይችላሉ። ረዳት ሰራተኞቻችን የሚሰሩት በሙሉ ጊዜ ተቀጣሪነት አይደለም። ሆኖም ቀጠሮ በመያዝ ማግኘት ይቻላል። በገዛ ቋንቋዎ ለመጠቀም አስተርጓሚ ከፈለጉም በስልክ ቁጥር 131 450 በመደበኛ የስልክ ጥሪ ክፍያ አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ። ከደወሉ በኋላ ለሚፈልጉት ቋንቋ አስተርጓሚ እንዲቀርብሎት ይጠይቁና በመስመር ላይ ይጠብቁ። አስተርጓሚው ሲመጣ የእኛን ስልክ ቁጥር እንዲደውልሎት ይንገሩት በዚህ ሁኔታ በራስዎ ቋንቋ በአስተርጓሚ ሊያናግሩን ይችላሉ።

ይህ ጽሁፍ በእንግሊዝኛ እና በሌሎች የኰሚኒቲ ቋንቋዎች በድረ ገጻችን (ዌብ ሳይት) ላይ ይገኛል www.mhahs.org.au

ጠቃሚ መገናኛዎች ዘዴዎች

  • በስልክ አስተርጓሚ ከፈለጉ በመ መርያ 131 450 ይደውሉ ከዚያም ኦፐሬተሩን/ሯን ከሚከተሉት ስልኰች አንዱ እንዲደውልሎት ይጠይቁ፡
  • ሄች አይ ቪ መረጃ ስልክ: 02 9332 9700 ወይም 1800 451 600
  • ACON: 02 9206 2000
  • ሲድኒ ሴክሹዋል ኽልዝ ሴንተር: 02 9382 7440